የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር ስማችን እንዲከበር ፊርማ በመፈረም አስተዋፅዖ ያደረጋችሁትን ሚድዋይፎች በሙሉ እያመሰገነ ቦርዱ ጠቅላላ ጉባኤና ፅ/ቤቱ ባደረጉት ያላሠለሠ ጥረት የሙያው ስያሜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በዕለተ ሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም 85ኛ ዓመት ቁጥር 309 በወጣው ህጋዊ ስያሜ ታትሞ ስለወጣ እንኳን ደስ አላቹሁ እያልን፡- ስያሜው በሁሉም እርከኖች የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተፈፃሚ እንዲሆን ቅጅውን በማተም እንድታሰረጩ በየመ/ቤታቹ በዞን በክልል እንድታስተዋውቁ እና እንድታስተባብሩ ጥሪ እናደርጋለን፡፡





